በአለም ዋንጫ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ኢንርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በድጋሚ ልትፈተን ነው።
ሚያዚያ 27, 2007

 ለረጅም አመታት በአፍሪካም ሆነ በአለም አቀፍ  የእግር ኳስ ማህበር ተወካይ አጥታ የቆየችው ሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአህጉራችን አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ወሳኝ ወንበር ከማግኘት ጀምሮ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ የእግር ኳስ ውድድሮችን እንዲመሩ ኢትዮጵያዊ ዳኞችን እስከማስመረጥ የደረሰ ለውጥ አሳይታለች።  በዳኝነቱ ረገድ ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ የተለያዩ የአፍሪካ ጨዋታዎችን በብቃት መዳኘት ችለዋል። ከሴት ዳኞቻችን ውስጥ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ  የተለያዩ  የአፍሪካ  የክለብ ጨዋታዎችን በብቃት ከመዳኘቷም በተጨማሪ በቅርቡ ካናዳ ላይ ለሚደረገው የሴቶች የአለም ዋንጫ ፊፋ እጩ ዳኛ አድርጎ መርጧት እንደነበር የሚታወስ ነው።
Lidiya

 ነገር ግን አሁን ከፊፋ ጋር ግንኙነት ካላቸው ምንጮቻችን በደረሰን መረጃ መሰረት ሊዲያ ባልታወቀ ምክንያት የፊዚካል ፈተና በድጋሚ እንድትወስድ ፊፋ ወስኗል። የመጨረሻ ፈተናውን ለመስጠት በዜግነት ሴኔጋላዊ የሆኑ የፊፋ ባለሞያዎች በ15 ቀን ውስጥ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፈተናው ሊዲያ ኢትዮጵያን ወክላ በአለም አቀፉ መድረክ ጨዋታዎችን ለመምራት የሚኖራትን እድል የሚወስን ይሆናል። እንደ ሊዲያ ሁሉ የካናዳውን ጨዋታ እንዲመሩ  ከሁሉም አህጉራት ከተመለመሉ የሴት ዳኞች ውስጥ የተወሰኑትን በተለያየ ምክንያት በድጋሚ የመጨረሻ ፈተና እንዲወስዱ መወሰኑም ታውቋል።

ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ  ፈተናውን በብቃት እንድትወጣው የኢትዮጵያ የስፖርት ቤተሰብ ምኞትና ተስፋ ነው። ዝግጅት ክፍላችንም በዚህ አጋጣሚ ለኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ  መልካም እድል እንዲገጥማት ይመኛል። 

ከፊፋ የመጣውን  ውሳኔ በበለጠ ለማጣራት ሪፖርተራችን የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ልኡልሰገድ በጋሻውን እና ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም። በተጨማሪም የፌዴረሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡን ጠይቀናቸው ስለጉዳዩ ምንም አይነት መረጃ እንዳልደረሳቸው ነግረውናል።

ፈለቀ ደምሴ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Abebe Girma [990 days ago.]
 I hope she will pass successfully. Let the help of God be with her.

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

ermias [990 days ago.]
 she will pass

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!