ዋልያዎቹ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ማክሰኞ ይጫወታሉ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና የአል ሜሪክ ጨዋታ ተሰረዘ።
መጋቢት 20, 2007

የኢትዮጵ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ማክሰኞ ከኢትዮጵ ቡና ጋር እንደሚጫዎት ከኢትዮጵና ቡና እግር ኳስ ክልብ የደረሰን መረጃ አመለከተ። የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ስራ አሰኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዱ ለኢትዮፉትቦል ዶት ኮም በስልክ እንደገለጹት የወዳጅነት ጨዋታው ጥሪ የቀረበው ከፌዴሬሽኑ ነው። ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ባንችልም የሁቱ ቡድኖች ጨዋታ እንዲካሄድ የተወሰነው የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ለፌዴሬሽኑ ባቀረቡት ጥያቄ ምክንያት ነው።
EthiopiaCoffee To Play against the Walyas

በሌላ ዜና ቅዱስ ጊዮርጊስና የሱዳኑ ኤል ሜሪክ ሊያካሂዱት የነበረው ጨዋታ መሰረዙ ተገለጸ። ለጨዋታው መሰረዝ ምክንያቱ የሱዳኑ ክልብ በአገር ውስጥ ውድድር መበመጠመዱ መሆኑን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። 

በዚህ አጋጣሚ ኢትዮ ፉትቦል የጨዋታውን ውጤት በቀጥታ LiveScore በዌብሳይቱ እንዲሁም በአንድሮይድ አፕልኬሽኑም እንደሚያስተላልፍ ለውድ የድረ ገጹ ታከታታዮች ለመግለጽ ይወዳል።

ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!